Tender Detail

Tender Details

  • Company Gurage Zone Finance Development
  • Address Wolkite Town : Gurage Zone : Ethiopia, Phone: 0113300112
  • Website
  • Deadline10 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 100,000 (CPO ወይም ቢድ ቦንድ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Categories Carpets And Curtains

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት G+9 ህንፃ አገልግሎት የሚውል መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Gurage Zone Finance Development


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት G+9 ህንፃ አገልግሎት የሚውል መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው ፣
  4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ተጨራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም ፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር መያያዝ አለበት ፡፡
  8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸው፣
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ወይም ማስያዝ አለባቸው፣
  10. ተጫራቾች ከላይ ለተገለፀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በጉ/ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ ማስገባት አለባቸው ፣
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጐ በዚህ ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፣
  13. የጨረታው ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ቢድቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም መሰራት አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  15. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው ቀን የሚሸጋገር መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

ማሳሰቢያ:- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Gurage Zone Finance Development seeks curtains for its G+9 office building via open tender. Bidders need a valid trade license, tax payment proof, TIN, supplier registration certificate, and VAT registration if the purchase exceeds ETB 500,000. Samples and detailed item specs required.
Save Tender