የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ቅጽ 1.የጽሕፈት መሣሪያዎች
- ቅጽ 2.የፅዳት ዕቃዎች
- ቅጽ3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ/ VAT የሚቆርጡ/ እና TIN ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በ15ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ፍርድ ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡
- ፍርድ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
- ፍርድ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡
- የሚቀርቡትን ዕቃዎች አይነት /ናሙና/ ዘወትር በሥራ ሰዓት መ/ቤታችን ድረስ ማምጣት ይችላሉ፡፡ /ማንኛውም ናሙና ኦሪጅናል መሆን አለበት/ ፡፡
- ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ያደርጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋዩ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ብር 4000/አራት ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ የተያዘው የተመሰከረለት ሲፒኦ ውሉ መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ይቆያል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍጹም አይቻልም፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ለተጨማሪ መረጃ:- 0911082154 /0912348437
የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
✨ messages.ai_summary
Kura Jida Sub-city District Court seeks suppliers for office supplies, stationery, cleaning materials, and electronics via open tender. Bidders must hold a valid business license, be tax-compliant, VAT-registered with TIN, and registered as suppliers with the Ministry of Finance or relevant authority.
