የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/07/2019
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም የ90 ቀናት በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ረፋድ 4:30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 5:00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36/0911-15-60-36
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise seeks to purchase electrical materials via open tender. Bidders must hold a renewed legal business license in the sector, provide proof of tax payment, a VAT payer certificate, and commercial registration, and be registered on the suppliers list.
