Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline26 Nov 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4ኛ (CPO፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateህዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም ምዝገባው እንደተጠናቀቀ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የቦሌ ሰሚት ሳይት ብሎክ 028 የቤት ቁጥር 24 ባለአንድ መኝታ ኮንደሚኒየም የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ሙሉነሽ ወንድሙ እና በፍ/ባለዕዳ መርዓዊ አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 195045 በ8/4/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/211118 በ15/10/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ሰሚት ሳይት ህንጻ ብሎክ 028 የቤት ቁጥር 24 ባለአንድ መኝታ የሆነ ኮንደሚኒየም በቁጥር በ/ሰሚ028/4310/03 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 47.1 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,853,950 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ፈ/ጽ/ቤት ስም c.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A one-bedroom condominium (Block 028, House No. 24, Bole Summit Site, 47.1 sqm) is being sold at auction by the Federal Courts' Judgment Execution Office. Bidders must deposit 25% of the starting price via CPO and may inspect the property beforehand.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender