Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline26 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (ብር 463,071) C.P.O
  • opening dateህዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም ምዝገባው እንደተጠናቀቀ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የሚገኙ 42.12 ካ.ሜ አራት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች (ቁ.837) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ወ/ሮ መስከረም ከበበው እና በፍርድ ባለእዳ እነ አቶ አየለ ሚደቅሳ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 189587 በቀን 14/09/2017ዓ.ም 205251 በቀን 7/4/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 837 የካርታ ቁጥር የካ/176538/05 በሟች ወ/ሮ ብርቱካን ወ/ማርያም ስም የተመዘገበ ከሆነው ይዞታ ውስጥ ከዋናው ቤት ከጀርባ በኩል የተሰሩ የሟች አቶ ተፈራ መርጋ እና የሟች ወ/ሮ ብርቱካን ወልደማርያም የውርስ ሀብት የሆነ አራት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች 42.12ካ.ሜ ሲሆን የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 1,852,284.00( አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 17 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction of four service rooms (42.12 sq.m) behind the main house on plot no. 837, Yeka Sub-city Woreda 04, inherited property. Bidders must deposit 1/4 of the starting estimate as a CPO; the winner must pay the full price within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender