Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline02 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 50 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 20,000 (CPO ወይም ቢድ ቦንድ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4:30
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ለሦስተኛ ጊዜ፡ በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦች ሽያጭ - የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የንብረት ማስወገድ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በመጋዘን የተጠራቀሙ ጋዜጦችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ለሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ታሽጎ 4:30 ላይ በመስሪያ ቤቱ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ንብረቶችን ማንሳት ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በሌላው ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማስገባት አይችልም፡፡
  6. ድርጅታችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-08-80-99 ወይም 0913-21-50-37
አድራሻ:- 4 ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency seeks to sell newspapers accumulated in its warehouse via open bid. Any interested bidder may participate by presenting a copy of identification. The agency reserves the right to cancel the tender in part or fully.
Save Tender