በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥጨረታ መለያ ቁጥር 00/2019ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ሎት - 1 የደንብ ልብስና ስፌት፣ ሎት- 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ሎት -3 የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት - 4 የህትመት ስራዎች ሎት-5 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ ሎት-6 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ሎት-7 የጥገና እቃዎች & ሎት-8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የላብራቶሪ ማሽኖች ሰርቪስ ፣የጀነሬተር ሰርቪስ እና የሞተት መኪና አገልግሎት መ/ቤቱ ባወጣው ስፔስፍኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በማንኛውም ግልጽ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 የደንብ ልብስና ስፌት ብር 36,000.00 ሎት 2 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 38,000.00 ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ብር 17,000.00 ሎት 4 የሕትመት ሥራዎች ብር 34,000.00 ሎት 5 አላቂ የሕክምና ዕቃዎች ብር 239,452.00 ሎት 6 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር18,000.00 ሎት 7 የጥገና ዕቃዎች ብር10,000.00 ሎት 8 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ብር 240,000.00 ሎት 9 የላብራቶሪ ማሽኖች ሰርቪስ፣ የጀኔሬተር ሰርቪስ ብር 20,000.00 ሎት 10 የሞተት መኪና አገልግሎት ብር 2,000.00 - የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር / በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 51 አየቀረቡ መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር /ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ሰዓት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እና በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው በተጨማሪም ብሮች /በማንዋል/ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ:-እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
አድራሻ:- ለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ አያት አደባባይ አለፍ ብሎ ወደ አራብሳ በሚወስደው አስፓልት ዞን 5ት መንገድ 12 በኮዶች መግቢያ መንገድ 1500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር:- 0910513885
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Lemi Kura Sub-City Woreda 03 Meri Health Center seeks bidders for 10 lots: uniforms/sewing, consumable office supplies, cleaning materials, printing, consumable medical supplies, miscellaneous items, maintenance materials, fixed office items, lab/generator service, and vehicle service. Bidders need a valid business license, tax clearance, MoF registration, VAT certificate, and prior-tender compliance.
