Tender Detail

Tender Details

  • Company Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251-12-49-28
  • Website
  • Deadline31 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ኮድ በተቀመጠው መጠን (CPO)
  • opening date21/02/2019 ዓ.ም 4:00 (ሐራጁ ይጀምራል)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 03/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት:-
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 03/2019 በ21/02/2019 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ግላሶችና ከቨሮች ፣ የእጅ ሰዓቶች ፣ ስፔርፓርቶች፣ የአይታ ዕቃዎች/ መነፅሮች፣ የመሬት ምንጣፍ፣ ኮስሞቲክ እና መዋቢያዎች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የስፖርት መሥሪያ መሣሪያዎች ፣ ኳስ፣ የተለያዩ አርቲፊሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥርን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል፡፡
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው፡፡
  3. በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ውድአነድ ቢሮ በመቅረብ ብር100 በመክፈል አንድ ለመግዛት ዘወትር በሥራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ዕቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነና ግቢ ነው፡፡
  5. ለሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ዕቃዎች በኮድ የተከፋፈሉ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራች በሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም " ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በሐራጅ ጨረታ ለመጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያው መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2:00 ሰዓት ምዝገባ ጀምሮን እንደተጠናቀቀ በ4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን በተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
  12. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746)

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Dire Dawa Customs Branch Office is selling assorted inherited goods by auction, including clothing, electronics, shoes, cosmetics, construction materials, stationery, sports items, and more. Bidders must provide a valid trade license, VAT registration, tax clearance, and ID. Goods are coded and bids must be pre-VAT.
Save Tender