የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Southwest Education Bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር - ት/ቢ/ግ/ጨ/- 01/19
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም -
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ
- ከግብርና ታክስ ዕዳ ነጻ የሆነ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ታርጫ ከተማ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኢ.ን.ባ. በቢሮዉ ሂሳብ ቁጥር 1000785238684 በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እያንዳንዱ ዕቃ ዓይነት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ :- በስልክ ቁጥር 0473450715 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Southwest Ethiopia Peoples' Regional State Education Bureau seeks bidders for the supply of stationery and consumable office materials via open tender. Eligible bidders must have a renewed business license, TIN, VAT registration, supplier registration, and no tax debt. Samples required for each item.
