Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline18 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1/4ኛ ብር 1,106,820 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ)
  • opening dateህዳር 9 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የኤልሳ ሰለሞን እና የማቲዎስ ኢታባ የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ፡ የ2019 ሞዴል ሀዩንዳይ ቱክሰን መኪና በ4,427,280 ብር የሐራጅ መነሻ ዋጋ ለሽያጭ የቀረበ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ኤልሳ ሰለሞን እና የፍ/ባለዕዳ ማቲዎስ ኢታባ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/212469 በቀን 29/07/2018ዓ/ም እና በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/216162 በቀን በ26/8/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦት የመኪናማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁ /ኮድ 3-B50008 አ.አ ቱክሰን የ2019ዓ.ም ምርት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 4,427,280 (አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ )ብር ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 4 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.216162 በቀን 3/2/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሕራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,106,820 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CP.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም c.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 2019-model Hyundai Tucson (code 3-B50008) is being sold at auction by the Federal Courts' Execution Office in a case between Elsa Solomon and Mathewos Itaba. Bidders must deposit 25% of the starting price via CPO at the Commercial Bank of Ethiopia; the buyer pays transaction tax.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender