Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ጅግጅጋ ከተማ ፡ ሶማሌ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913220473
  • Website
  • Deadline29 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityሐራጅ ብር 500,000፤ ግልጽ ጨረታ የመጫረቻ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening date19/02/2019 ዓ.ም 4:00 (ግልጽ) / 4:15 (ሐራጅ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ ለስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


ግልጽ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ ለስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች 17/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች:--

  1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፡፡
  2. ለሐራጅ ጨረታው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ዕቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ለሐራጅ ጨረታ ተጫራች የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል።
  5. ለግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት።
  7. ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
  8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
  10. ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጂጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
  11. ተጫራቹ ዕቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 17/02/2019 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በጅግጂጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ19/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:45 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው 19/02/2019 ከጠዋቱ 4:15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡

N.B:- አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Jigjiga Customs Office is selling confiscated contraband goods—electronics, home décor, construction materials, clothing, spare parts, cleaning supplies, food items and more—via auction and open bid. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration, tax payment proof and ID. Winners pay 15% VAT.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender