በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሠመራ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AFSDG-01/2019
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሠ ንግድ ፈቃድ
- ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- በመንግስት አቅራቢነት የተመዘገበ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያለው
- ተጫራቾች በየሎቱ ወይም በሚወዳደሩበት ዕቃዎች 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የፋይናንስ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ በሚያቀርበውን የእቃዎች ዋጋ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከዚሁ መመሪያ ጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋውን ከነናቱ ሞልቶ ከላይ የተጠቀሱትና ማስረጃዎች አሟልቶ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሠመራ የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት የሚዘጋ ሆኖ በእለቱ ከጠዋቱ 4:30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምክንያት በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋር ዘላቂ ልማት ግቦች ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሠመራ
✨ messages.ai_summary
The Afar SDG Project Coordination Office seeks bidders for the supply of office supplies and furniture through open tender AFSDG-01/2019. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, TIN certificate, and government supplier registration.
