Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አጠገብ ያለው ቢሮአችን ሦስተኛ (3) ፎቅ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-58-07
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100 (በአክሽን ኢትዮጵያ)
  • Bid Securityየሰጡት ዋጋ 5% (CPO፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ)
  • opening date20/02/2019 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) እና የኮንስትራክሽን ማቴርያል በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-07/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) እና የኮንስትራክሽን ማቴርያል በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) በለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ:-
    ተ.ቁ የእቃው አይነት የጨረታው አይነት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት ስልክ ቁጥር
    1 አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) ግልፅ 13/02/2019 20/02/2019 4:00 4:30 0221118429/ 0222118925
    2 የኮንስትራክሽን ማቴርያል ግልፅ 13/02/2019 20/02/2019 4:00 4:30 0221118429/ 0222118925
  5. በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የኢትዮጵያ አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
  6. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያስፈትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት የኮንስትራክሽን ማቴርያል በአዳማ ከተማ በሬፓ አክባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እንዲሁም አዳዲስ አልባሳት (ቦርሳዎች) በአዳማ ቀርቆር አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 3፣4 እና 5 ውስጥ ሲሆን ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል ።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፀው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
  12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11- 5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ:- አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Adama Customs Branch is selling seized new clothing (bags) and construction materials by open auction. Bidding is exclusively via the Auction Ethiopia app or www.auction.et. Bidders need a relevant renewed business license, VAT registration, tax clearance and recent VAT activity certificate, TIN and document purchase receipt. Importers or their family members may not participate.
Save Tender