Tender Detail

Tender Details

  • Company Semera Customs Branch Office (ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሰመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 366 2302
  • Websitehttp://www.ecc.gov.et/
  • Deadline30 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityግልጽ ጨረታ የዋጋው 5%፤ ሐራጅ በምድብ ከብር 10,000 እስከ ብር 200,000 (CPO)
  • opening date20/02/2019 ዓ.ም 3:45 (ግልጽ) / 4:00 (ሐራጅ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 04/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Semera Customs Branch Office (ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 04/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ ዘርፍ የጨረታው ዓይነት ዕቃው ያለበት ቦታ
1 የፅዳት ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
2 ኮስሞቲክስ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
3 ምግብ ነክ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
4 ኤሌክትሮኒክስ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
5 ኮስሞቲክስ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
6 ጫማ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
7 የእጅ ሰዓቶች ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
8 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
9 ፓኪንግ ማሽን ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን
10 መለዋወጫዎች ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈቅድ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡ በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1:00- 5:00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ የመንግሥት ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው መለዋወጫዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ኮስሞቲክስ(ምድብ 01) ብር 50,000(ሀምሳ ሺ ብር)፣ ኮስሞቲክስ (ምድብ02) ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር)፣ ጫማ (ምድብ01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ ጫማ (ምድብ 03) ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ኤሌክትሮኒክስ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ የእጅ ሰዓቶች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና(CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSON SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
    ተ.ቁ የቅ/ጽ/ቤቱ ስም የጨረታው አይነት የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
    1 ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግልጽ ጨረታ እስከ 19/02/2019 20/02/2019 ዓ.ም 3:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 3:45 ሰዓት ይከፈታል
    2 ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሐራጅ ጨረታ እስከ 19/02/2019 20/02/2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ይከፈታል
  5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ:- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ያስያዙት ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለባቸው ሲሆን ይህን ባይፈጽሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመንግሥት ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርገው በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሱ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጡ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመንግስት ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
  8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% የሚከፍሉ መሆኑ ይታወቅ፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ:-0332401510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Semera Customs Branch Office invites bids for the public and auction sale of various confiscated goods, including cleaning supplies, cosmetics, food items, electronics, shoes, watches, packaging machines, spare parts and miscellaneous goods, stored at the government warehouse in Semera Dry Port. Bidders must submit a valid trade license, VAT registration, TIN and tax clearance; VAT registration is waived for items priced under 500,000 birr.
Save Tender