የተለያዩ እቃዎች ግዥ፣ አገልግሎቶች እና እድሳትና ጥገና ስራዎች (ብ.ግ.ጨ/01-2019) - ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የእቃ ግዥ እና እድሳትና ጥገና ስራዎች ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር:- ብ.ግ.ጨ/01-2019ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የSub Structure ስራዎች ማለትም excavation & earth work,Masonry,Concrete work,Elevation Wall,Glazing work,Roofing work,Metal work,Carpentry & Joinry,Finishing ስራዎችን ግንባታ እና የተለያዩ እቃዎችን ማለትም የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የህትመት ስራ፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የትራንስፖርት መኪና ኪራይ፣ Office Machine Maintenance and Full-service፣ ለሶፍትዌር ልማትና ስልጠና፣ የሶፍት አገልግሎት መኪና ኪራይ፣ ፕላንት ማሽነሪ መሳሪያ፣ ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ተያያዥ ቁሳቁሶች እቃ ግዥ፣ ለህንፃ ለቁሳቁስ እድሳትና ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ሎት | የሚገዛው እቃ ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን በብር |
| 6211 | የደንብ ልብስ | 8,000 |
| 6212 | አላቂ የቢሮ እቃዎች | 5,500 |
| 6213 | የህትመት ስራ | 1,500 |
| 6214 | አላቂ የህክምና እቃዎች | 2,500 |
| 6215 | አላቂ የትምህርት እቃዎች | 8,100 |
| 6218 | የፅዳት እቃዎች | 5,600 |
| 6232 | የትራንስፖርት መኪና ኪራይ | 2,500 |
| 6243 | Office Machine Maintenance and Full-service | 5,000 |
| 6255 | ለሶፍት አገልግሎት መኪና ኪራይ | 2,000 |
| 6313 | ፕላንት ማሽነሪ መሳሪያ | 9,250 |
| 6314 | ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ተያያዥ ቁሳቁሶች እቃ | 5,000 |
| 6344 | ለህንፃ ለቁሳቁስ እድሳትና ጥገና | 2,500 |
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይፈለጋል።
- ተጫራቾች ቲን ነበር ሰርተፍኬት፣ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ክሊራንስ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢነት ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው መጠን እና ሎት (ምድብ/ክፍል) በባንክ የተረጋገጠ CPO የጨረታ ማስከበሪያ በተቋሙ ስም Temenja yazh G/Secondary School ማቅረብ አለባቸው። ይህን የማያሟላ ተጫራች በቀጥታ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የማይመለስ 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን በአስረኛው ቀን 11:00 ተዘግቶ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል።
- በያንዳንዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወይም ገፅ ወይም ሎት ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ክብ ማህተም እና ፊርማ በማኖር ማስገባት ይኖርባቸዋል። ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ህጋዊነትን እና ኦርጅናልነትን ለመለየት ስለማያስችል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የሚመዘኑበት በሀጋዊነት፣በፍላጎት መግለጫ፣በቴክኒክ ዋጋ እና በናሙና መሰረት ሲሆን ጨረታ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የለውም። ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ እና የፋይናንሻሉን ኮፒ በሌላ አንድ ተጨማሪ ፖስታ በማሸግ፣ በአጠቃላይ በሁለት ፖስታ ብቻ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ይህን ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- የህትመት ስራን በተመለከተ ውሉ የሚፀናው ለ2019 በጀት ዓመት ብቻ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት በዚሁ በጀት ዓመት እንደአስፈላጊነቱ የህትመት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት።
- የ Office Machine Maintenance and Full-service ስራዎች በግልፅ ጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠየቀው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ውሉ የሚፀናው ለ2019 በጀት ዓመት ብቻ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት በዚሁ በጀት ዓመት እንደአስፈላጊነቱ Office Machine Maintenance and Full-service የመስጠት ግዴታ አለበት።
- ለትራንስፖርት አገልግሎት እና ለሶፍት አገልግሎት ውሉ የሚፀናው ለ2019 በጀት ዓመት ብቻ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት በዚሁ በጀት ዓመት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት።
- እድሳትና ጥገና ስራዎች በተመለከተ ከተራ ቁጥር 1 ጀምሮ የተዘረዘሩት መስፈርቶች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የጨረታ አሸናፊ በአጠቃላይ በሚያቀርበው ዋጋ ድምር ውጤት ይለያል።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ:- ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት በአምባሳደር ሬስቶራንት በስተጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0114703178 ይደውሉ።
ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
✨ messages.ai_summary
Tsehayna Yazh General Secondary School seeks suppliers for various goods, services and maintenance works, including sub-structure construction, clothing, office/medical/educational/cleaning supplies, printing, vehicle rental, office machine maintenance, software services, plant machinery, and building materials repair. Bidders must submit TIN, trade registration, renewed license, VAT, clearance and supplier certificates.
