Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅሳይ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
  • Address Hawassaa Ethiopia, Phone: ---
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (ብር 1,196,600)
  • opening date10/03/2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ የሚገኝ 1000 ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ - የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅሳይ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በአፈፃፀም ከሳሾች እነ ወ/ሮ ርቢት ኤርሚያስ 9 (ሰዎች) እና በአፈፃፀም ተከሳሾች እነ አቶ ብርሃኑ ተከሌ 4 (ሰዎች)መካከል ስላለዉ የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር ቀበሌ ውስጥ በሟች ወ/ሮ ሙሉ ተከሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በካርታ ቁጥር D269A270 የቦታ ስፋት 1000 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመና/ከ/ከ/ልማትና ኮ/ን/ጽ/ቤት በላኩት መነሻ ግምት ዋጋ ብር 4,786,400.00 (አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር) ሆኖ በሐራጅ እንዲሸጥ እና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ 09/02/2019ዓ/ም ጀምሮ እስከ 09/03/2019ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ የሀራጅ ሽያጩ በ10/03/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡ ስለሆነም:-

  • በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 030 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ።
  • ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
  • በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  • ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሔድበታል።
  • ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የስም ዝውውር በፍ/ቤቱ ትእዛዝ ይፈፀምለታል፡፡ የጨረታው ሒደት የሚካሔደው 10/03/2019ዓ/ም 4:00 - 6:00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ገበያ ዳር ቀበሌ ውስጥ በሟች ወ/ሮ ሙሉ ተከሌ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቅጥር ግቢ እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 1,000 sq.m residential property in Hawassa, Lake Side sub-city, registered under the late W/ro Mulu Tekele, is being sold by public auction per Hawassa High Court order. Bidders must deposit 25% of the starting price at the court and present the receipt to participate.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender