የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ተኝተዉ ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ተኝተዉ ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ያላቸዉ የግብር መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ስር የተደራጁ ተጫራቾች ቫት ያልተመዘገቡ ከሆነ በገቢዎች ባለስልጣን ዕዉቅና ባለዉ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የሚገለገሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 5000.00 (አምስት ሺ)ብር የያዘ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ብር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ኮፒ ና ኦርጅናል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከተታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የጊንር አጠቃላይ ሆስፒታል የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለ መኖር ጨረታ ሰነድ እንዳይከፈት አይከላከልም ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0946319866/0975407902
ይውለው ይጠይቁ፡፡
የጊንር አጠቃላይ ሆስፒተል
✨ messages.ai_summary
Ginir General Hospital seeks bidders to supply food for inpatients through an open tender. Eligible bidders need a valid business license, tax payment proof and TIN; VAT registration is required, with an alternative receipt rule for MSEs. Bidders must submit copies and originals in separate envelopes.
