ኦዳ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለጸውን አንድ ደረቅ ጭነት ፒክ አፕ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Oda Share Company
ኦዳ አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ኦዳ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለጸውን አንድ ደረቅ ጭነት ፒክ አፕ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተሽከርካሪው ዝርዝር መረጃ
| ተ.ቁ. | የመኪናው አይነት | ዝርዝር | ብዛት |
| 1 | ቶዮታ ደረቅ ጭነት ፒክ አፕ መኪና | ደረቅ ጭነት ፒክ አፕ | 1 |
በመሆኑም
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፍቃድ ያላቸው(ለድርጅት ከሆነ)፤
- የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል&
- ግለሰብ ከሆን የታደሰ የቀበለ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ያላቸው፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከተውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ ያልቀረበ ተጫራች በውድድሩ አይሳተፍም፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን 7ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 30,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት በታሸገ ፖስታ ኡራኤል አካባቢ የሚገኘው አዋሽ ኢንሹራንስ ሕንፃ የኦዳ አክሲዮን ማህበር 7ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ ማቅረብ የሚቻል መሆኑን እየገለፅን፤ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በ11ኛው በቀን 21/02/ 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ ሆኖ የሚከፈተው ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይሆናል::
- ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኡራኤል አካባቢ የሚገኘው አዋሽ ኢንሹራንስ ሕንፃ
የኦዳ አክሲዮን ማህበር 7ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል
ስልክ ቁጥር +251912656209
✨ messages.ai_summary
Oda Share Company is selling by tender one Toyota dry-cargo pickup truck. Eligible bidders must be businesses with a renewed trade license, TIN and VAT registration certificate, or individuals with a renewed ID and TIN, and must submit these documents.
