Tender Detail

Tender Details

  • Company Misrak Poly Technic College (የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address 22 ማዞሪያ ከትራፊክ ጽ/ቤት ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከአስፋልቱ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከአዲስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-18-09-14
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityበየሎቱ ከብር 2,000 እስከ 90,000 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ በ4:30 ሰዓት
  • Categories Textile, Garment & Leather , Software Provision, Development And Web Design , Stationery Materials

የስልጠናና የቢሮ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ (17 ሎቶች, 001/2019) - የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Misrak Poly Technic College (የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019

የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ግብዓት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እና የቢሮ ዕቃዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት፡-

የሎት ቁጥርየግዥው ዓይነትየጨረታ ማስከበሪያ መጠን
ሎት 1የፅህፈት አላቂ ዕቃዎች35,000.00
ሎት 2የፅዳት አላቂ ዕቃዎች32,000.00
ሎት 3የደንብ ልብስ አላቂ ዕቃዎች30,000.00
ሎት 4የኮንስትራክሽን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች50,000.00
ሎት 5ቢዩልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች60,000.00
ሎት 6የቴክስታይል ጋርመንት አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች90,000.00
ሎት 7የሌዘር አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች70,000.00
ሎት 8የአውቶሞቲቭ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች40,000.00
ሎት 9የአይሲቲ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች80,000.00
ሎት 10የእንጨት ስራ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች75,000.00
ሎት 11ማኑፋክቸሪንግ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች40,000.00
ሎት 12የፀጉር ስራ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች20,000.00
ሎት 13የሆቴል ኪችን አላቂ ዕቃዎች5000.00
ሎት 14ከተማ ግብርና አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች10,000.00
ሎት 15ህትመት3000.00
ሎት 16ለህፃናት ማቆያ2000.00
ሎት 17ህክምና አላቂ ዕቃዎች2000.00
  1. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣ በአቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ግዥ ዳይሬክቶሬት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለያንዳንዱን ሎት በተናጠል የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ዋጋ የሚሰጡት ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ሲሆን በራሳቸው ሰነድ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ድርጅት ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂነቱን ባለቤቱ ይወስዳል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በየሎቱ በተጠየቀው መሠረት በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ምሥራቅ ፖ. ቴክኒክ ኮሌጅ /Misrak Polytechnic College/ በሚለው ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረምና የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በየገፁ በማድረግና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተሸጣላቸው ሰነድ ላይ ብቻ በግልፅ በታሸገ ፖስታ ለየብቻው ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በፖስታዎቹ ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በመሙላት የአስተዳደር ሕንፃ አንደኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ መሳተፍ የምትፈልጉ ከጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት በኮሌጁ ስም በቀረበ ጊዜ የተገደበ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በየንግድ ዘርፋቸው ብቻ መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡ ከንግድ ዘርፋቸው ውጪ የሚጫረቱ ድርጅቶችን ኮሌጁ አያወዳድርም ለሚጫረቱት እያንዳንዱ ነጠላ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
    ሎት 1፣2፣3 ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ ከሦስት ቀን በፊት ጀምሮ ናሙናውን ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ዕለት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    -በኮሌጁ የሚዘጋጅ ናሙና ሲኖር በግልፅ ቦታ የሚታይ ሲሆን ሌሎች በዕቃው ዝርዝር መግለጫ መሰረት የሚወዳደሩ ናቸው፡፡
  8. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ቡድን አባላት እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ4:30 ሰዓት ግዥ ዳይሬክቶሬት የአስተዳደር ሕንፃ ምድር ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ 60 ቀን ይሆናል፡፡
  10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ከትራፊክ ጽ/ቤት ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከአስፋልቱ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከአዲስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 0116-18-09-14/0116-18-19-49/0116-18-08-01 0913-98-29-52/0948001301

የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Misrak Poly Technic College invites open bids for 17 lots of consumable and fixed training and office supplies, covering stationery, cleaning, uniform, construction, electrical, textile/garment, leather, automotive, ICT, woodwork, manufacturing, hairdressing, hotel/kitchen, urban agriculture, printing, childcare and medical items. Bidders need a valid business licence, tax and VAT registration, and supplier registration.
Save Tender