Tender Detail

Tender Details

  • Company የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 222 14 79
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityለሎት-1 ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/፣ለሎት-2 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening dateጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል
  • Categories Machinery , Electrical Materials

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ዋናው መ/ቤት) ለጋራዥ እና ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 05/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር


ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NCB WWC 05/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ዋናው መ/ቤት) ለጋራዥ እና ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 05/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ተ.ቁየሎት ቁጥርዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goodsመለኪያብዛትምርመራ
1ሎት-1Difference types of Welding machineበቁጥር02
2ሎት-2Difference types of Electrical materialsበቁጥር/ሴት/ሜትርጥቅል

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/፣የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት።ተጫራቾች እነዚህንና ልሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ88 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት-1 ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/፣ለሎት-2 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ/ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል/ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. .በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር- 058222-14-79 መጠየቅ ይቻላሉ።
  8. ማሳሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጂ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ።

አድራሻ፡-

ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106
ስልክ ቁጥር 0582221479

✨ messages.ai_summary
The Water Works Corporation seeks legal firms to supply welding machines (Lot 1) and electrical materials (Lot 2) for drinking water projects in Garazh and Debre Markos University. Bidders must hold a renewed business license, TIN, VAT registration, and commercial registration certificate.
Save Tender