የዋና መሥሪያ ቤት ነባር ሕንፃ 1ኛና 2ኛ ፎቅ የኢፖክሲ ወለል ንጣፍ ሥራ (GC 5/BC 4, 029/19) - ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 029/19
ድርጅታችን ዋናው መሥሪያ ቤት የነባሩ ሕንፃ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ሥራ ክፍል ወለል በኢፖክሲ የወለል ንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች እንዲሁም ደረጃቸው GC 5 ወይም BC 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነዱን በሲዲ በድርጅቱ አዲሱ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት በድርጅቱ 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የፋይናንሸያልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 8/3/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሸያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ሰነድ ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር፡-011-1-55-52-30
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
