የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት – የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስና ጫማ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ግዥ (ሎት 1–7)
የሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 4 ቋሚ እቃ (ፈርኒቸር)፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅና አልባሳት፣ ሎት 6 የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 7 የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የወጣውን ማስታወቂያ በማየት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እገልጻለን፡፡
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያለው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጂናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በC.P.O ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ፤ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻው ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮምቦልቻ ከተማ ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከጥቅምት 10/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሀሰና አገር ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ10/02/2019 ዓ.ም እስከ 20/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በቀን 20/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ ዓይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻው ከ 5 ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0975854015 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ40 ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ፣ ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል፡፡
- ለሎት 5 እና ለሎት 6 አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት በሚያቀርበው ናሙና ወይም ሳምፕል መሰረት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
- ከሎት 5 እና ከሎት 6 ውጭ ያሉ ሎቶች ላይ መስሪያ ቤቱ ሳምፕል ያስፈልጋቸዋል ብሎ የሚያምንባቸው አይተሞችን በሚቀርበው ናሙና ወይም ሳምፕል መሰረት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሀሰና አገር ክፍለ ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ክፍለ ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሀሰና አገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Hasena Ager sub-city office in Kombolcha seeks suppliers for stationery, cleaning supplies, electronics, furniture, uniforms/clothing, shoes, and vehicle spare parts across lots 1–7. Bidders need a valid trade license, tax clearance, TIN, and VAT registration if the purchase exceeds ETB 500,000. Bids must be complete per lot; samples may be required.
