ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
My Wish Enterprise (ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
MY WISH ENTERPRISE
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ የውስጥና የውጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የተሽከርካሪው አይነት እና ሞዴል | የተሰራበት ሀገር እና ዘመን(እ.ኤ.አ) | ታርጋ ቁጥር | ሞዴል | ሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የጨረታው መነሻ ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) | ብዛት |
| 1 | ኪንግ ሎንግ አውቶቢስ እስከ 11 ሰው የሚጭን | ቻይና 2012 | አአ-03-01-A03834 | ኪንግ ሎንግ ሚኒቡስ | LA6PAAA23DB502325 | F60QAC00167 | 690,409.99 | 01 |
| 2 | ሊፋን አውቶሞቢል 4 ሰው የሚጭን | ቻይና 2012 | አአ-03-01-91882 | Lifan 360 | LCN64ED5XC0015384 | LFB479Q*12100357* | 1,081,653.27 | 01 |
| 3 | ሊፋን አውቶሞቢል 4 ሰው የሚጭን | ቻይና 2014 | አአ-03-A06773 | Lifan 530 | LLVZAZA19G0280565 | LF479Q3B*14300146 | 558616.1685 | 01 |
| 4 | ሊፋን አውቶሞቢል 4 ሰው የሚጭን | ቻይና 2012 | አአ-03-91401 | Lifan 620 | LLVZA3A29C0223004 | LF481Q3*120502346* | 685729.4865 | 01 |
| 5 | ሊፋን አውቶሞቢል 4 ሰው የሚጭን | ቻይና 2013 | አ-03-93337 | Lifan 520 | LLV2A2A1300063445 | LF479Q3*120802256* | 481384.6295 | 01 |
- ማንኛውም ፍላጎቱ ያለው ድርጅት/ግለሰብ የድርጅቱ ሰራተኞችና ባለድርሻዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- አንድ ተጫራች ለአንድና ከአንድ በላይ ተሽከርካሪዎች መጫረት ይችላል::
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4:00 ሰአት ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ተሽከርካሪዎቹን መመልከት ይችላሉ::
- ተጫራቾች መጫረት ለሚፈልጉት ተሽከርካሪ ከላይ በሰንጠረዡ የተገለጸውን የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት፣ የሚገዙበትን ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢ ሰነድ ውስጥ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ለውድድር አይቀርብም::
- ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 4:00 ላይ ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች በተገኙበት ከቀኑ በ4:30 ላይ ይከፈታል::
- ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ድርጅቱ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በማስታወቂያ ያሳውቃል:: የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከድርጅቱ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ7 (ሰባት) የስራ ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል:: ከላይ በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል::
- ከስም ዝውውር፣ ከማጓጓዣና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ወጪዎችን አሸናፊው ይሸፍናል::
- በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወዲያውኑ ተመላሽይደረጋል::
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ከመብራት ሃይል ወደ ኃይሌ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ዋና /ቤት
ለበለጠ መረጃ: በ 0911-31 88 56 ወይም 0911-40 05 76 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
My Wish Enterprise is selling used vehicles by open bid: a King Long minibus (11 seats) and four Lifan cars (4 seats each), sold as-is. Any interested organization or individual may bid, including the enterprise's own employees and shareholders, and bidders may bid on one or more vehicles.
