ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል::
Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፡
የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ
ቁጥር:: ፀኢ/ግንአ/004/2019
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት፣ ኩባንያው የቢሮ ዕቃዎችን (ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የኮምፒውተርና የሰርቨር ዕቃዎችን ወዘተ) እና የተለያዩ የኩባንያውን ሰነዶች በጥንቃቄ በማሸግ፣ በመጫን፣ በማጓጓዝ እና በማውረድ/በማደራጀት የተረጋገጠ ልምድ ያላቸውን ብቁ ድርጅቶች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
ከተጫራቾች የሚጠየቁ መስፈርቶች:
- ተጫራቾች ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት የ5 ዓመት ልምድ እና አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና የማሸጊያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ አቅም ሊኖራቸው ይገባል::
- ተጫራቾች ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የሥራ መርሃ ግብር ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ: ተጫራቾች 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው::
- አገልግሎት ሰጪው በእንቅስቃሴው ሂደት ለሚደርስ የሰነድ መጥፋት ወይም ጉዳት የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል::
የጨረታ ሂደት:
- የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ ከጥቅምት 09/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- የጨረታ ማስረከቢያ: የተሟላ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ መክፈቻ: ጨረታው ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- የኩባንያው መብት: ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የቢሮቹን ጉብኝት: ተጫራቾች የሁለቱንም ሕንፃዎች አቀማመጥ እና የሚዛወሩ ዕቃዎችን አይነትና መጠን ለመገምገም የሚያስችል የቅድመ-ጨረታ የጉብኝት ፕሮግራም ከ09/02/2019 -15/02/2019 በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል::
አድራሻ:- ፀሐይ ኢንሹራዝስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣
የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ: +251 111 119 70 / +251 116 50 66 30
✨ messages.ai_summary
Tsehay Insurance seeks qualified firms to pack, load, transport and unload office items (tables, chairs, computers, servers, etc.) and documents for its head office relocation. Bidders need a valid trade license, tax compliance, 5 years' similar experience, vehicles and packing materials, a work schedule, and insurance coverage for loss/damage.
