Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline17 Nov 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityአምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO)
  • opening dateበተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • Categories Architectural And Construction Design , Road And Bridge Construction , Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ /ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለሚሰራው የድንጋይ መፍጫ ማሽኖች መትከያ ቦታ ዝግጅት ፣ ዲዛይን እና ግንባታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T654

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ /ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (Category-1 Road/General Construction) በጨረታ አወዳድሮ በ ሎት 1 – በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ፣ ኮኪ ናሲብር ቀበሌ ኮምቦሎቻ አጥቢያ ፣ ሎት 2 – ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ጊምቢቹ ወረዳ፣ ኮኪ ናሲባር ቀበሌ ፣ አፍላሚ አጥቢያ እና ሎት 3 - ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱከም ክፍለ ከተማ ወረዳ፣ አቡሴራ ቀበሌ፣ ጋርቢ መንደር ለሚሰራው የድንጋይ መፍጫ ማሽኖች መትከያ ቦታ ዝግጅት ፣ ዲዛይን እና ግንባታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-1 ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ በ90 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ለአንድ፣ ለሁለት ወይም ለሁሉም የጨረታ ክፍሎች (Lots) መወዳደር ይችላሉ፣ ነገር ግን ከአንድ (1) የጨረታ ክፍል በላይ አይሰጣቸውም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 8 / 209 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (200.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T654 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢ.ሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማሰያዝ አለባቸው፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ መቶ ሃምሳ ቀናት (150) ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ኅዳር 8/ 2019 ዓ.ም ከቀኑ እስከ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር Tel: +251 115 17 4028/8025
ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group seeks eligible Grade 1 Road/General Construction contractors to prepare, design and build foundations for stone-crushing machines across three lots in North and East Shewa zones. Bidders may compete for one, two or all lots but can win only one.
Save Tender