ኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ፈፅም ይፈልጋል፡፡
Kolfe Keranyo Sub City Design and Construction Work Administrative and Finance Pool Office (የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ሥራ አስተዳደርና ፋይናንስ ፑል ጽ/ቤት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2019
ኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ተለያዩ ግዥዎችን በፑሉ ተጠቃሚ ለሆነ መ/ቤቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በ12ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ ፈፅም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 የግብርና ግብዓቶች
- ሎት 3 የዕዳት እቃዎች
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፤ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት ተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር ያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በኢንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ሠዓት ድረስ ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4:30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሎት 13 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ቀኑ 4 ሰአት ድረስ ብቻ ናሙና ማቅረብ /ግዴታ ወደ ፅ/ቤታችን ሳንፕል ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ በተዘጋጀው ስፔክ መሰረት መሙላት የሚገባቸው ሲሆን ጨረታው እንደተከፈተ ስፔኩ ታይቶ ሲረጋገጥ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል፡፡ ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ኮ/ቀራኒዮ ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301
ስልክ ቁጥር፡- 0118350897
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፑል የመንግሰት ግዥ ቡድን
✨ messages.ai_summary
Kolfe Keranyo Sub City invites open bids for supplies/services in 12 categories, including uniforms, agricultural inputs, and cleaning equipment. Bidders may bid for all or some lots and must submit renewed business license, TIN, supplier registration, and VAT registration. Samples required for listed lots.
