በኢፌዴሪ ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ(ብረታ ብረት)፣ የምርት ግብአት፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች ግዥ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ኮማማኢ/ሰፄማ/001/2018
በኢፌዴሪ ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የግዥ አይነት፡-
- በሎት 1 ጥሬ ዕቃ(ብረታ ብረት)
- በሎት 2 የምርት ግብአት
- በሎት 3 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች
የተጫራቾች መመሪያና ግዴታ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ.
- የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN NO ያላቸዉ.
- ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸዉ።።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተዉ የሚቀርቡት ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነዉ።።
- ማንኛዉም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።።
- የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር ከ00/100) በመክፈል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘዉ ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ላይ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበዉ ዝርዝር በመሙላት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ ኢንዱስትሪዉ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።።
- የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል።።
- ጨረታዉ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል።።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት በኋላ በሦስት ቀን ዉስጥ ቀርቦ ዉል በመዋዋል ንብረቱን በኢንዱስትሪዉ ቅጥር ግቢ ማቅረብ አለበት።።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ኦርጅናሉንና ኮፒዉን ለየብቻ በፖስታ አሽገዉ ማቅረብ አለባቸዉ።።
- ኢንዱስትሪዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነዉ።።
- አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘዉ ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0923801915/0981702770 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።።
ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
✨ messages.ai_summary
Ethio-Engineering Group's construction machinery manufacturing industry invites bids for: Lot 1 raw steel/metals; Lot 2 production inputs; Lot 3 stationery, cleaning and safety items. Bidders need a renewed trade license, TIN, and VAT registration certificate. Submit original and copy separately; prices only on the provided form.
