በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት የፋ/ጽ/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት የፋ/ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ሴክተር ጽ/ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ
- ሎት 01 አላቂ የቢሮ የጽፈት መሳሪያዎች ፤- ለጨረታ ማስከበሪያ 41,538.00 CPO የሚያዝ
- ሎት 02 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፤ - ለጨረታ ማስከበሪያ 183,012.00 CPO የሚያዝ
- ሎት 03 የተለያዩ የደንብ ልብሶች ፤ለጨረታ ማስከበሪያ 98,418.00 CPO የሚያዝ
- ሎት 04 ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ፤ለጨረታ ማስከበሪያ 11,107.00 CPO የሚያ
- ሎት 05 የተሽከርካሪና መጓጓዣ እድሳት፤ ለጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 CPO የሚያዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በዚሁም መሠረት :-
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት በዘርፉ ቀጥተኛ የሆነና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለቸው::
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ አምራች ድርጅት መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ካልሆነም በሃገር ውስጥ ምርት ላይ መሰማራታቸውን ማቅረብ አለባቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number / ያለው ::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ኪሊራንስ ማቅረብ የሚችልና፣ በወቅቱ በማንኛውም ሁኔታ ያልተቀጣ (እንዳይወዳደር ያልታገደ)መሆን አለበት ::
- የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ::
- በማንኛውም ምክንያት ከአቅራቢነት ያልታገዱ ::
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በጨረታ ማስታወቂያ በተሰጠው የጨረታ ማስከበሪያ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ስም CPO በማሰራትና ማስገባት ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እና ናሙና ለሚስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ በሃርድ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ያንዱን ዋጋ ፤ጠቅላላ ዋጋ እና ድምሩን በትክክል ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ሰነድና ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አውቃችሁ በጥንቃቄ በመሙላት ኦሪጂናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በወረዳው ግዢ የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሦስተኛ ፎቅ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ::
- ተጫራቾች በሎቱ ያስገቡትን ጠቅላላ ድምር በጥንቃቄና ትክክለኛውን ማስቀመጥ አለባቸው::
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታው ከአቃቂ ዋናው ንግድ ባንክ ጀርባ በሚገኘው ጽ/ቤት ወይም በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ ሦስተኛ ፎቅ ፋ/ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ 4:30 ሰዓት ይከፈታል:: 11 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-34-54-90 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Akaki Kaliti Sub-city Woreda 3 Administration seeks to purchase various goods for its sector offices via open tender, in five lots: office stationery, cleaning supplies, uniforms, miscellaneous office supplies, and vehicle/transport maintenance. Bidders need a valid business license, TIN, VAT registration, and must submit samples where required.
