Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው ¼ (1ኛ ብር 31,796,332.61፤ 2ኛ ብር 5,073,662.50) CPO
  • opening dateምዝገባ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በአቃቂ ቃሊቲ ቀበሌ 10 የሚገኝ G+3 ጋራዥ/የኢንዱስትሪና መኖሪያ ህንፃዎች (1700 እና 1635 ካ/ሜ) እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ የቤት ቁ. 822 (500 ካ/ሜ) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትከኪሏ ወልደየስ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ መገርሳ በዳዳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/86951 በ10/12 ቀን 2004 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/201443 በ24/4/2005 ዓ/ም በ18/10/2010 ዓ/ም በሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት

  • 1ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቀበሌ 10 ክልል በተጠሪ ስም የተሰራ በጋራዥ ድርጅት የመኪና ማቆሚያ ያለው G+3 ያለው (ግራውንድ ፕላስ ስሪ) የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ ህንፃ በካ/ቁ/AA000070701085 የተመዘገበ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 67,887,100 (ስልሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ብር) በካ/ቁ/AA000070701050 የሐራጅ መነሻ ዋጋ 59,298,230.44 (ሀምሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር 44/100) ጠቅላላ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 127,185,330.44 (አንድ መቶ ሀያ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ብር 44/100) በካ/ቁ/AA000070701085 የተመዘገበው የቦታው ስፋት 1700 ካ/ሜ የቤቱ አይነት ለኢንዱስትሪ የህንፃው ወለል ከፍታ G+0 እና G+3 የሆነ በካ/ቁ/AA000070701050 የተመዘገበው የቦታው ስፋት 1,635 ካ/ሜ የቤቱ አይነት ለመኖሪያ የህንፃ ወለል ከፍታ G+0 ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ሲሆን ካፒታል ጌን ግራ ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
  • 2ኛ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ቀበሌ 09/43 የቤት ቁጥር 822 የሆነ ቤት ከነሰርቪሶች ና ማድቤት የሆነ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 500 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 20,294,650 (ሃያ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ካፒታል ጌን ግራ ቀኙ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ¼ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction of two properties: a G+3 garage/industrial building on 1,700 sqm and a residential building on 1,635 sqm in Akaki Kaliti, plus a 500 sqm house with services in Nifas Silk Lafto. Bidders must deposit 25% of the starting price via CPO; winners pay the balance within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender