ድጋሚ፡ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤ.ቁ.515 (171.19 ካ/ሜ) ሰነድ አልባ ቤት የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አብዮት ታደሰ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ህጻን ቃሉ በላይነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.183566 በቀን 16/02/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ መሰረት እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.193332 በቀን 24/3/2016 ዓ.ም ትዕዛዝ መሰረት ፍርድ ያረፈበት ቤት የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ውስጥ የሚገኝ የቤ.ቁ.515 ካርታ የለውም ሰነድ አልባ ነው ቤቱ ይዞታው ከቀበሌ ቤት ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ ያለ ሲሆን የይዞታ ስፋት ከቀበሌ ቤት ጋር ጠቅላላ 236 ካ/ሜ ሲሆን የግለሰቡ ይዞታ ቤት ያረፈበት 131.48 ካ/ሜ ሲሆን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው በጠቅላላው 171.19 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ 5,960,508.26 (አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሺህ አምስት መቶ ስምንት ከ26/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.193332 በቀን 04/06/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እና በኮ/መ/ቁ.193332 በቀን 20/09/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ 1/4ኛ 1,490,127.06 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ከ06/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ¼ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
