የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ግዥ
- ሎት 02 የጽሕፈት መሣሪያዎች ግዥ
- ሎት 03 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 04 የተሽከርካሪ / የመኪና /ዕቃ መለዋወጫ ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ በግብር ከፋይነተ ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን የምዝገባ ወረቀት እንደዚሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የውል ማስከበሪያ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ክፍያ በሚፈጸምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት፡፡
- ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድሩ በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል
- የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467710688 መጠየቅ ይችላሉ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Region Bureau of Education seeks suppliers for office-use materials via open tender, split into four lots: electronics, stationery, cleaning supplies, and vehicle spare parts. Bidders must hold a valid business license, trade registration, tax ID, and VAT registration, with current tax compliance evidence.
