የጽህፈት መሣሪያ፣ አላቂ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ሞተር ሣይክልና መለዋወጫ ግዥ (ኮዞፋመ-ግጨ/ዕአግ/001-5ጨ/-2019) - የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ቁጥር(ኮዞፋመ-ግጨ/ዕአግ/001-5ጨ/-2019)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በመንግስት መደበኛ ገንዘብ እና ካፒታል ገንዘብ ምንጭ ከዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሰበሰበው የግዥ ዕቅድ ፍላጎት መሠረት፡- የጽህፈት መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ፣የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች እና የሞተር ሣይክል ግዥ እና የሞተር መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ላይ አሻሽለዉ ያወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 71/2017 አንቀጽ 55 በንዑስ አንቀጽ 1፣2 እና 3 መሠረት በነዚህ ሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ እንዲሁም በመደበኛ ጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠየቁትን መሠረታዊ ነጥቦች ወይም የህግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ህጋዊ ግብር ከፋዮች/አቅራቢዎችን/ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በሙሉ፡-
- 1/ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ
- 2/ በዘርፉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ
- 3/ በዘርፉ /TIN Number/የግብር ከፋይነት የምስክር ወርቀት ያላቸዉ
- 4/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- 5/ በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወርቀት ያላቸዉ
- 6/ ማህበራት ከሆኑ ህጋዊ የሰዉነት ማረጋገጫ ምስክር ወርቀት ያላቸዉ
- 7. ማህበራት መደራጀታቸውን የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ህጋዊ የድጋፍ ዳብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- 8/ ተጫራቾች፡- የጨረታ ዝርዝር ወይም መደበኛ የጨረታ ሠነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ የሠነድ ሽያጭ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ 500/አምስት መቶ ብር /በመክፍል ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ.11 በመቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- 9/ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ሠነድ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ /CPO/ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለጽ/መሣሪያ፣ አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 30,000/ሠላሳ ሺህ ብር/ ለፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ 30,000/ሠላሳ ሺህ ብር/፣ የሞተር ሣይክል ግዥ 30,000/ሠላሳ ሺህ ብር/ እና የሞተር ሣይክል መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር በፖስታ አሽገዉ ለኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ብሎ በአድራሻ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- 10/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በአንድ ኤንቬሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና 1 ኮፒ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ጋር በትክክል በታሸገ በአንድ ኤንቨሎፕ ወይም የእናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ማህተም በማሳረፍ፣ አድራሻ በመግለጽና በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- 11/ ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 6፡00 ላይ ታሽጎ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ አከፋፈትን በተመለከተ የቴክኒካል ኦርጅናል ፖስታ በመጀመሪያ ደረጃ ይከፈታል፡፡ በጨረታ ማስታወቂያ መሠረት የተቀመጡ ቴክኒካል የግምገማ ከተገመገመ በኋላ ቀጥሎ የፋይናንሻል ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ በመመሪያ መሠረት ተከፍቶ ይነበባል የተደረገዉ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ጥናት ጋር በማመሳከር ግምገማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- 12/ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ የማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- 13/ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሰነድ 10% በማስያዝ ባሸነፉበት የስራ የዉል ማስከበሪያና ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ይዘዉ ቀርበዉ 15 ስራ ቀናት ዉስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ውርስ ሆኖ በግዥ አዋጅና አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ለጥፋተኝነት ሪፖርት ይቀርባል፡፡
- 14/ ተጫራቾች ጨረታ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይዉላል፡፡ ጨረታዉ ይከፈታል በተባለዉ በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 15/ ተጫራቾች ተሚልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም፡፡
- 16/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 17/ ተጫራች የጨረታ ሠነድ ዋጋ ማቅረቢያ እንዲሁም ከመደበኛ የጨረታ ሠነድ በተጨማሪ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ቸር ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-/09 06 48 25 47/09 16 14 00 71 /09 20 98 00 15 ደወለዉ ይጠየቁ
የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ -ካራት
✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies, consumables, electronics, furniture, motor vehicles and spare parts for Konso Zone Finance and Plan Development Department. Open to licensed, tax-compliant suppliers and cooperatives meeting registration, TIN, VAT and sector requirements.
