የካፍቴሪያ ኪራይ አገልግሎት (አ/ቢ/መ/ስ/ት/ስ/ማ/ጨ/ቁ/001/2019) - የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር የአበበ-ቢቂላ መ/ስ/ት/ስ/ማ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር አ/ቢ/መ/ስ/ት/ስ/ማ/ጨ/ቁ /001/2019
የጨረታ ሠነድ መመሪያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር ለሚገኘው የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ትምህርት ስልጠና ማእከል በ2019 በጀት ዓመት የካፍቴሪያ አገልግሎት ለሚያቀርቡ ተጫራቾች በግቢው ውስጥ ያለውን ካፍቴሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የዘመኑ የታደሰና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሣቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)/ ቲኦቲ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በ"አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር ለሚገኘው የአበበ-ቢቂላ መታሰቢያ ስፖርት ትምህርት ስልጠና ማእከል ስም በተሰራ C.P.O ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ /ፖስታ/ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
- የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸውን የመወዳደሪያ ሃሳብ እያንዳንዳቸውን በፖስታው ላይ በግልጽ /በማስፈር / ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከየአበበ-ቢቂላ መታሰቢያ ስፖርት ትምህርት ስልጠና ማእከል ፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ /አገልግሎት/ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ 1 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፤ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጭ ያደርጋል
- ተጫራች አሸናፊ ድርጅቶች ለሚያቀርቧቸው የውሉን ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም (CPO) ያስይዛሉ፡፡
- የጨረታ ሣጥን በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ
- የቤት ኪራይ ነጻ ነው፡፡
- የካፍቴሪያ መገልገያ ዕቃዎች በሙሉ በመስሪያ ቤቱ የሚሟሉ ይሆናል፡፡
- የውሃ እና መብራት አገልግሎት በነፃ ይሆናል፡፡
- ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚከራየው ህንፃ በቢሮው በሚገኘው የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የመዝናኛ ካፍቴሪያውን በአካል በመምጣት መመልከት ይችላሉ፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት የምግብ ዝርዝሮች በተጨማሪ የምግብ ዓይነት ማስገባት ከፈለጉ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከነዋጋው ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር የአበበ-ቢቂላ መ/ስ/ት/ስ/ማ
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Youth and Sport Bureau, under the Abebe Bikila Memorial Sport Education and Training Center, seeks to rent out its cafeteria through open competition. Bidders must hold a valid business license, be registered in the suppliers list, have paid taxes, and be VAT/TOT registered. The contract period must be at least one year.
