መድሃኒት፣ የላብራቶሪና የህክምና እቃዎች፣ አላቂ፣ የፅዳት፣ ማሽነሪና የህንፃ ጥገና ግዥ (10 ሎቶች, 0008/2019) - ልደታ ክ/ከተማ የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 0008/2019
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፀዉ መሰረት እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለዚህም ከዚህበታች የተዘረዘሩት የጨረታ ማስከበሪያ / የጨረታ ዋስትና የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /CPO /ብቻ ማስያዝ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
| ሎት | የበጀት ኮድ እና የዕቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
| 1 | 6211 መድሃኒት እና የላብራቶሪ ዕቃዎች | 40,000 |
| 2 | 6212 አላቂ ዕቃዎች | 8000 |
| 3 | 6213 አላቂ ዕቃዎች | 6000 |
| 4 | 6214 ህክምና እቃዎች | 80,000 |
| 5 | 6218 የፅዳት እቃዎች | 20,000 |
| 6 | 6219 ልዩ ልዩ እቃዎች | 400 |
| 7 | 6233 መስተንግዶ | 10,000 |
| 8 | 6244 የህንፃ ጥገና | 11,000 |
| 9 | 6313 ለፕላንት ማሽነሪ ና መሳሪያ መግዣ | 60,000 |
| 10 | 6314 ለሕንፃ ፣ተገጣጣሚዎች መግዣ | 56,000 |
በዚህም መሰረት፡
- በጨረታዉ ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ /ማቅረብ ላለባቸዉ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት /በመንግስት ግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢያ ዎ ምዝገባ አምራቾች ያላቸዉ /አምራች የሆናቸዉ/ብቻ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /የጨረታ ዋስትና የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን/እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በተ/ሃ/ማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ/በፖስታ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት በተ/ሃማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀ/w ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ነገርግን በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው በአስረኛ ቀን እስከ አስራአንድ ሰዓት /11፡00 ድረስ ብቻ ነው ፡፡ ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ ማስገባት አይቻልም፡፡ አስራ አንደኛ /11ኛ/ቀን ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል /3፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት የላብራቶሪ እቃዎች እና ሎት1፣ ሎት 2፣ሎት3 ፣ሎት4፣ሎት5 ፣ሎት 7፣ሎት9 እና ሎት 10 ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ /ስርዝ ድልዝ ያለው ጨረታ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- አሸናፊ ተጨራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ጤና ጣቢያችን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ስልክ ቁጥር፡- 011 5 51 09 57 /011 5 57 69 78 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተ/ክለሃይማኖት ቅርንጫፍ ወረድ ብሎ ጎላ ፓርክ አጠገብ ተ/ክለሃይማት ጤና ጣቢያ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፡፡
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Teklehaymanot Health Station seeks suppliers for medicines, laboratory and medical supplies, consumables, cleaning materials, machinery and building maintenance across 10 lots. Bidders need a renewed business license, tax compliance, supplier registration, TIN and VAT certificates; samples required for specified lots.
