Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline16 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4 (ብር 668,873.61) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Disposal Sale

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁ. 407 (53.94 ካ/ሜ) የሐራጅ ሽያጭ (መነሻ ብር 2,675,494.44) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ትዕግስት በቀለ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አሬጋሽ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/18933 በ25/10/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/113218 በሐምሌ 25 ቀን 2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 407 በፋይል ቁጥር 008420 የካርታ ቁጥር አከ-08/2711/3407/ ኢካርታ በተመስገን ቱንጋ እና የዘለቀ ተካ ወራሾች ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋቱ በሰነድ 45.94 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 53.94ካ/ሜ የሆነ በአካባቢው የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2ካ/ሜ ይነካዋል አዋሳኞቹ በስተሰሜን ቤት ቁጥር 410 በስተደቡብ መንገድ /ባዶ ቦታ በስተምዕራብ መንገድ/ባዶ ቦታ በስተምስራቅ ቤት ቁጥር 408 የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,675,494.44 ( ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አራት ብር ከ44/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 53.94 sq.m house (No. 407) in Addis Ketema Sub-city, Woreda 06, is offered for auction sale by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit 1/4 of the starting price via CPO and pay transaction tax. The property can be inspected beforehand.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender