Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline16 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4 (ብር 421,481.92) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Disposal Sale

በሸገር ከተማ ሰበታ (ፉሪ ክ/ከተማ) የሚገኝ 200 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ (መነሻ ብር 1,685,927.67) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እንዳለ በዛብህ እና የፍ/ባለዕዳ መሰለች ሲሳይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/93166 በየካቲት 28 ቀን 2011 ዓ/ም እና የፌ/መ/ደ/በኮ/መ/ቁ/146672 በ04/03/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ክ/ከተማ ሰበታ ከተማ በአዲሱ ፉሪ ክ/ከተማ ቀበሌ 02በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት በሊዝ የሚተዳደር የቦታ ስፋት 200ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,685,927.67 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ብር ከ67/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction sale of a 200 sq.m leasehold house in Sebeta (Furi), Oromia. Bidders must deposit 1/4 of the starting price via CPO from Commercial Bank of Ethiopia; the winner must pay the full amount within 15 days. Transaction tax is paid by the buyer.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender