Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline16 Nov 2026, 11:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4 (ብር 11,105,167.49) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CPO
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Disposal Sale

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ 694.88 ካ/ሜ ቤት (ድርጅት) የሐራጅ ሽያጭ (መነሻ ብር 44,420,669.95) - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፀፀም ጽ/ቤት

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አለም መካ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ወልዴ በረካ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/102803 በ2/10/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ11/11/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ14/5/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በቀድሞ 25 በአዲሱ 13 ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ወ13/ውዝ01/66/2199/00 የቤት ቁጥር 001 የሆነ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የቦታ ስፋት 1,247.46ካ/ሜ ሲሆን በአስኮ ሚኪሊ ላንድ መንገድ ፕሮጀክት ምክንያት በከፊል የፈረሰ እና ካሳ የወሰዱ እና ከ1,247.46 ካ/ሜ ላይ 448.76 ካ/ሜ የተቀነሰባቸው ቢሆንም በ39/40ኛ ዙር መንገድ ጥናት እና በአስኮ ሚኪሊላንድ መንገድ ፕሮጀክት ዲዛይን መሻሻሉ ምክንያት ካሳ ያልተከፈላቸው እና 2ኛ ዙር የሚቀነስባቸው የቦታ ስፋት 103.82ካ/ሜ የሚቀነስባቸው ሲሆን ቀሪው የቦታ ስፋት694.88ካ/ሜ ቤት ድርጅት ስለሆነ ካፒታል ጌን ታክስ የሚከፍለው የፍ/ባለዕዳ ሲሆን ገዥው አካል ቤቱን የሚረከበው የክ/ከተማው መሬት አስተዳደር በላከው እስኬች መሰረት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 44,420,669.95 ( አርባ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ከ95/100 ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A 694.88 sq.m house (organization) in Addis Ketema Sub-city Woreda 13 is auctioned via execution sale. Buyer pays transaction tax; capital gains tax is the debtor's. Bidders must deposit 1/4 of the starting estimate as a verified CPO via Commercial Bank of Ethiopia.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender