ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ህጋዊ የግል ትራንስፖርተሮችን በተባባሪነት በማስገባት/Sub Contract/ የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ለአንድ ዓመት ውል በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡
Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ
ጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/002/2019
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ህጋዊ የግል ትራንስፖርተሮችን በተባባሪነት በማስገባት/Sub Contract/ የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ለአንድ ዓመት ውል በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች በተመለከተ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት/ Tax clearance/
- በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin)
- ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የመንግስት ግዥ ባለስልጣን የተመዘገቡበት (Egp Regstration)
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ዲፓርትመንት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው የአገልግሎት ግዥ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አስቀድሞ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኦፕሬተር የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ያላቸውና ኮፒው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጭነት አገልግሎት መስጠቱን የሚያረጋግጥ/የሚገልጽ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ከሶስት እና ከዚያ በላይ ድርጅት የተሰጠ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ተሽከርካሪዎች አጠቃላይ የመድን ዋስትና የተገባላቸው ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ህጋዊ የባንክ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)፤ በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፤ ፋይናንሽያል ኮፒ በማድረግ ለይተው በተለያየ ፖስታ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- በቴክኒካል ፕሮፖዛል ግምገማ ያለፈ ተጫራች በፋይናንሻያል ሰነድ አከፋፈት ላይ እንዲገኝ ጥሪ ይደረግለታል፡፡
- የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ ተጫራቾች የታሪፍ ማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉት በውል ጊዜ ውስጥ የተደረገው የዋጋ ጭማሬ 20% እና ከዚያ በላይ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 400 ኩንታል የመጫን አቅም ያለውን ተሽከርካሪን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- በተጫራቹ የሚቀርበው ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ይሆናል፤
- የጨረታ ማቅረቢያ ሠነዶች በሙሉ በአማርኛ ቋንቋ ተፅፈው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በዛውኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፤ እንዲሁም በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ሣይገኙ ቢቀር ጨረታው ይከፈታል፤
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
የድርጅቱ የሥራ ሰዓት
✓ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት - 6፡00 ሰዓት
✓ ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ እስከ 10፡00
በስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027
ፋክስ 0114-39-63-36 ፖ.ሣ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Emergency Relief Transport Enterprise seeks dry cargo freight transport services for one year, engaging experienced legal private transporters as subcontractors through open bid. Bidders must have tax clearance, renewed business license, TIN, VAT registration, EGp registration, operator competency certificate, ownership proof (libre), and good performance records from three or more organizations.
