የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ሎት፡- 1 ልደታ የሚገኘውን የፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከል በኢትዮ ቴሌኮም ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ስማስደረግ ተፈልጓል::
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nominees PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/9/19
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር
ሎት፡- 1 ልደታ የሚገኘውን የፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከል በኢትዮ ቴሌኮም ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ስማስደረግ ተፈልጓል:: በመሆኑም የዕድሳት ስራውን ማከናወን የሚችሉ ደረጃ 5 እና በላይ ያላችሁ
ሎት 2፡- የውኃ ፓምፕ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በስም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በስም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል::
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2:00-6:00 እንዲሁም ከሰዓት 7:00-10:30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን (ጠዋት 2:00-6:00) ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) እንዲሁም ለሎት 2 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4:30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል::
