Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
  • Address የምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-660-0088
  • Website
  • Deadline27 Oct 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityየንብረቱን መነሻ ዋጋ ሃያ በመቶ(20%) በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ክፍያ ማስያዣ/ሲ.ፒ.ኦ/
  • opening dateጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ በ4:00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  • Categories Machinery , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ የተረከበውን ንብረት ባለበት በድርድር ሽያጭ ጨረታ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

የድርድር ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ የተረከበውን ንብረት ባለበት በድርድር ሽያጭ ጨረታ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተከራዩ ስምየድርድር ሽያጭ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታየንብረቱ ዓይነትንብረቱ የሚገኙበት ቦታየድርድር ሽያጭ ጨረታ መነሻ ዋጋየደርድር ሽያጭ ጨረታው ደረጃየድርድር ሽያጭ ጨረታ ቀን እና ሰዓት
የወንድወሰን አላዛርየኢትዮጵጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍChemical Sprayerኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጉቶ ጊዳ ወረዳ፣ ነቀምቴ ከተማ208,372.50 (ሁለት መቶ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ከ50/100)2ኛጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ በ4:00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡

የድርድር ሽያጭ ጨረታ መመሪያ:-

  1. የድርድር ሽያጭ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፣
  2. የድርድር ሽያጭ ጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋሟት ወይም አነስተኛና መከከለኛ ኢንተርፕራይዝ) ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀ ሰነድ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ በማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ/በካሽ/ የሚገዙበትን ዋጋ፣ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. የድርድር ሽያጭ ጨረታው አሸናፊ መንግስት ከንብረቱ የሚፈልገውን ቀረጥ ከፍሎ ወይም ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እና ሌሎች ማናቸውንም ክፍያዎች በመክፈል ስመ-ንብረቱን ወደ ራሱ ማዛወር አለበት፡፡
  4. የንብረቱን መነሻ ዋጋ ሃያ በመቶ(20%) በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ክፍያ ማስያዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. በድርድር ሽያጭ ጨረታው ለተሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማስያዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. ለድርድር ሽያጭ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ላሸናፊው ተጫራች ከጠቅላላው ካሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው በራሳቸው ፈቃድ የድርድር ሽያጭ ጨረታውን/ግዥውን/ የተወወ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የድርድር ሽያጭ ጨረታው ይሰረዛል፤
  7. ንብረቱን ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል የእጅ በእጅ ሽያጭ ውል በመፈረም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ገንዘቡን ካልከፈለ የድርድር ሽያጭ ጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
  8. አስራ አምስት በመቶ/15%/ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም-ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
  9. ስለንብረቱ ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 057-660-73-47 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉም ካሉ ዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል፤
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የድርድር ሽያጭ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Nekemte District, seeks to sell repossessed property by negotiation sale auction for cash. Item: chemical sprayer, located in Oromia, East Wollega, Guto Gida, Nekemte. Open to individuals, institutions, or MSMEs. Bidders must buy the document for ETB 100 and submit a 20% CPO.
Save Tender