የበአታ ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች፣ የህክምና መገልገያዎችና የጥገና አገልግሎቶች ግዥ ጨረታ
የበአታ ጤና ጣቢያ
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓመት በጀት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1፤ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ ቋሚ
- ሎት 2፤ የደንብ ልብስ
- ሎት 3 ህትመት
- ሎት 4፤ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃዎች
- ሎት 5፤ የጥገና እቃዎች
- ሎት 6፤ የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 7፤ የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች
- ሎት 8፤ የሚወገድ የመድሃኒቶች በኪሎ
- ሎት 9፤ ሮቶ የጥገና አገልግሎት
በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የተጫረቱበትን ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲ.ፒ.ኦ በበንክ የተረጋገጠ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ዋና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር ቀን) ተከታታይ የስራ ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት ይኖረውም፡፡
- የጨረታውን አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሰረት ካላቀረቡት በግገር ህጉ መሰረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸውል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውም ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ላይ ተዘግቶ 3:30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት አድራሽ አራዳ ክ/ከተማ በአታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች በሎት 2-5 ያለው በሙሉ ኦርጅናል ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም 1፡ሎት1 ካታሎግ መስሪያ ቤቱ ድረስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃዎችን ሳምፕል እና ካታሎግ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውድቅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ከቅ/ስላሴ ቤተክርስቲያን ወደ ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት ወረድ ብሎ በስተምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ ከመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ነው፡፡
- ስልክ ቁጥር፡- 011-8699041, 011-8684810 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
የበአታ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Beata Health Station invites bids for various goods, medical supplies, and maintenance services under nine lots, including electronics, uniforms, printing, stationery, cleaning materials, maintenance items, tailoring, medicines, medical supplies, and rotto maintenance. Bidders must have a valid trade license, TIN, and VAT registration if applicable.
