የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች በ2019 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተው የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፣ ብትን ጨርቆችን፣ ጫማዎችንና ሌሎች የአደጋ መከላከያ ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የሠራተኞች ደንብ ስብስ ገዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ - 04/2019
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች በ2019 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተው የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፣ ብትን ጨርቆችን፣ ጫማዎችንና ሌሎች የአደጋ መከላከያ ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ድርጅቱ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል አዲስ አበባ ከተማ፣ ከቀበና ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ አይል ሊቢያ ማደያ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመታገዝ የደንብ ልብሱን ዝርዝር በማየት እያንዳንዱን ዕቃ/ልብስ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bid Bond Guarantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በጽሁፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
አድራሻ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤
አራዳ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07፣
ቀበና ኦይል ሊቢያ ከፍ ብሎ
ስልክ ቁ. 011-122-00-20
011-124-02-58
✨ messages.ai_summary
Oromia Forest and Wildlife Enterprise seeks to buy tailored uniforms, fabrics, shoes and other safety clothing for its staff, per the tender document. Eligible bidders must have a valid trade license, TIN, registration certificate, VAT registration and tax clearance.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
