Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላው ዋጋ 0.5% (ከ500,000 ብር በላይ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ) CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ
  • opening dateከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል
  • Categories Construction Machinery , Machinery Rental

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


ለመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር:-ሲ/መ/ባ/002/2019

የማሽን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁየማሽነሪ ዓይነትብዛትየአንዱ ሰዓትጠቅላላ ሰዓት
1ግሬደር58504,250
2ሮሌር58504,250

በዚሁ መሠረት:-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Un-conditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ በማሰራት ለብቻው በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የሚቀርቡ ማሽነሪዎች በሙሉ የፈረሰ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
  5. የሚቀርቡ ማሽነሪዎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ እና ከአንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላ ፕሮጀክት ማሽነሪዎችን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሸናፊው ድርጅት በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ወጪው በባለሥልጣኑ መ/ቤት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  6. የሚቀርቡ ማሽነሪዎች የኢንጂን ሠዓታቸው እና የነዳጅ አዲዮሜትር በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
  7. ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ማሽነሪዎችን ወደ ሥራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የማሽነሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በስም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ:- ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር:- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority seeks suppliers for rental of construction machinery (graders and rollers) for road construction in the region. Bidders must provide a valid trade license, tax clearance, VAT and TIN certificates, and supplier registration certificate. Machinery must meet engine-hour and fuel-meter requirements.
Save Tender