ድርጅታችን ለሁለት አመት የሚቆይ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብአት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 030/19
ድርጅታችን ለሁለት አመት የሚቆይ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብአት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል :: ስለሆነም ጠቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው::
ጨረታው በ10/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለጸ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል:: የፋይናንሻያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው:: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም::
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
