Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለመ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114708503
  • Website
  • Deadline21 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 100.00 (የማይመለስ፣ በኦንላይን)
  • Bid Securityከዋጋው 5% (CPO)
  • opening date11/02/2019 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች (መለዋወጫ፣ ሞባይል፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ አልባሳትና ሌሎች) የኦንላይን ሽያጭ (ማስታወቂያ ቁጥር 14/2019) - የጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች
ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 14/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም www.auction.et (አፕሊኬሽን) ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤

በመሆኑም

  1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ
  4. ከሀሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
    ተ.ቁየቅ/ጽ/ቤቱ ስምየጨረታው አይነትየንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
    1አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ ቤትየእቃ ግልፅእስከ 10/02/201911/02/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ሙሉ በሙሉ የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
  8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት፡- በስልክ ቁጥር 09-05-11-55-11

አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (አክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011 - 470 - 85- 03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Addis Ababa Kality Customs Branch Office invites bids to sell various seized, abandoned, and contraband goods, including vehicle spare parts, mobile phones and parts, electronics, home and office items, clothing, footwear, cosmetics, and more, via online auction. Bidders need a valid business license, TIN, VAT certificate, and tax payment proof.
Save Tender