በድጋሚ፡ ለባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ህትመቶች፣ ቲሸርት እና ባነር (አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/047/2026) - አማራ ባንክ አ.ማ
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
አማራ ባንክ አ.ማ
Amhara Bank S.C.
ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/047/2026
- አማራ ባንክ አ.ማ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ለሚያካሄደው የባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ለሚደረግ ሁነት ዝግጅት ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሱትን የተለያዩ አገልግሎት እና አቅርቦቶችን በብቃት መፈፀም የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ቁ.ጥ የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ 1 የተለያዩ ህትመቶች፣ ቲሸርት፣ እና ባነር ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ጠዋት 4፡30 ሰዓት 50,000.00 - ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ወለል ላይ ከጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ) የምድር ወለል ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲቲስ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-29-05/4491 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አማራ ባንክ አ.ማ
ከባንክ ባሻገር!
✨ messages.ai_summary
Amhara Bank invites eligible organizations to bid for various printed materials, t-shirts, and banners for its shareholders' annual general meeting. Bidders must submit a renewed business license, professional license, tax registration, VAT and tax clearance certificates. Incomplete submissions will be rejected.
