Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-551-50-04
  • Websitehttps://combanketh.et/
  • Deadline26 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (ሲፒኦ)
  • opening date16/02/2019 ዓ.ም 3:00 -4:00 ጠዋት
  • Categories Machinery , Sales, Disposals And Foreclosure , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል::

Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የሰሌዳ ቁጥር የንብረቱ አይነት የሞተር ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት
1 ራሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ ወንድም ፈለቀ አአ-02-C33705 ሃዩንዳይ ግራንድ i10 አዉቶሞቢል G4LANM14995 MALB241C8NM149028 3,098,304.00 16/02/2019 ዓ.ም 3:00 -4:00 ጠዋት
2 አለታ ላንድ ኩፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ ሀብታሙ ሲሳ ------ በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ ከተማ የሚገኝ የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ማሽነሪዎች ------ ------ 43,333,027.52 16/02/2019 ዓ.ም 4:00 -5:00 ጠዋት

በመሆኑም፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው::
  2. ሐራጅ የሚከናወነው አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ውስጥ ነው::
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል:
  4. ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸናፊ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል::
  5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል::
  6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይችላል:
  7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
  8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
  9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

✨ messages.ai_summary
Commercial Bank of Ethiopia invites bidders to an open auction of repossessed assets: a Hyundai Grand i10 automobile and plastic-products manufacturing machinery located in Hawassa, Sidama Region. Bidders or legal representatives may participate by depositing 1/4 of the starting price via CPO; CBE CPO preferred.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender