የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎችና የህትመት ግዥ - በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዶ/ር/አ/መ/መ/ጤ/ጣ
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎችን ለመፈፀምአቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሎት 1 -የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 -የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎ ት 3 -ህትመት
- 1.1 ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- 1.2. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- 1.3. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- 1.4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 ( አምስት መቶ ብር ) በመክፈል በዶ/አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- 1.5. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለያንዳዱ ሎት ብር 10000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም /CPO/ወይም (BIL BOND) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 1.6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 1.7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2፡30 እስከ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- 1.8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- 1.9. ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 1.10. የፅዳት እና ፅህፈት መሳርያዎች ናሙና ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ተወዳዳሪዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማስረጃ፡- በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ 0251-13-07-61 መደወል ይቻላል፡፡ ሞ/ል 0924124510
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዶ/ር አቤል መልካሙ መታሰብያ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Procurement of office stationery, various cleaning supplies, and printing, split into three lots, by Dr. Abel Melkamu Memorial Health Station under Dire Dawa Administration Health Bureau. Bidders must hold a valid trade license, be tax-compliant and VAT-registered, registered as government suppliers with TIN, and submit samples for cleaning and stationery items.
