የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ሙያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ብረታብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Police College (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ)
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ሙያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ብረታብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ አዳማ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው ላይ ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-
- የጨረታ ሰነድ የተዘጋጀው በኦሮሚኛ ቋንቋ ስለሆነ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ሊዩ ሊዩ ገቢዎች በሚለው ስም A/C ቁጥር 1000133792817 ላይ በማስገባት የጨረታ ሰነዱን በኮሌጅ ቅጥር ጊቢ ፋይናንስ ቢሮ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 10% ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሸጡ ብረታብረቶች አስመልክቶ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3፡00 ጀምሮ እስከ 10፡30 በአካል በሰንቀሌ (አምቦ) መደበኛና ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰዓት ተሸጦ የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት በይፋ በኮሌጁ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 09-11-90-95-86 እና 09-13-01-50-46
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Oromia Police College seeks to sell out-of-service steel and metal items via open bid. Bidders must buy the tender document in Oromiffa, submit technical and financial proposals separately, and include a 10% CPO. Items can be inspected in person at the Senkele (Ambo) institute.
