በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የበቆሎ መፍጫ ማሽን እና ህንፃ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁ.03/2019
የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.03/2019
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የበቆሎ መፍጫ ማሽን እና ህንፃ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁ.03/2019
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ሕጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት አግዲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ የበቆሎ መፍጫ ማሽን እና ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ለቆዳ ማምረቻ የተዘጋጀ ህንጻ ሞጆ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ጨረታው የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00 ሰዓት - 11:00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00 - 6:00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ለአንዱ ጨረታ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መሙላት ይችላሉ፡
| ተ.ቁ | የመ/ቤቱ ስም | ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት | የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን | የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ | የበቆሎ መፍጫ ማሽን | ማስታወቂያው መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት | ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
| 2 | ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ | የቆዳ ማምረቻ ተዘጋጀ ህንጻ 17,514.00 ካሬ ላይ ያረፈ | ማስታወቂያው መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት | ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3:45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
- 4. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- 5. የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 31ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
- 6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- 7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡
- 8. ከላይ በተ.ቁ 7 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- 9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-4010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia's Ministry of Revenue Adama branch invites bids to sell tax-debt-seized items: a corn grinder in Bishoftu and a leather-production building in Mojo. Bidders must submit ID copies and pay a non-refundable fee per lot.
